ከ33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑት የፌደራል ዋናው ኦዲተርና የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሚያዚያ 22 እና ግንቦት 6 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በቅደም ተከተል ሪፖርቶቻቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ በዋናው ኦዲተር የቀረበው የ2ዐዐ4 ዓ.ም በጀት ዓመት ኦዲት ሪፖርት በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ከሕግ ውጭ የተፈፀሙ ጉድለቶችን [...]
ከኢህአዴግ ተፈጥሮ የሚመነጨውን ሙስና ሥርዓቱን በመለወጥ እንጂ ዓመታትን ጠብቆ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በማሰር መግታት አይቻልም!!!
-
በጎጃም ህገወጥ እስርና አፈና ተባብሶ ቀጥሏል
በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ ሰዎች በግፍ እየታሰሩ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተለይ...
-
የምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ በቅዱስ ሲኖዶሱ ታገዱ
- እግዱ ከሙስና ጋር የተገናኘ ነው - ‹‹ሙስናው በአንድ ሀገረ ስብከት ብቻ አይደለም›› አገልጋዮች የምዕራብ...
-
ከእነ መላኩ ፈንታ እስር በስተጀርባ
ሁለት የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ12 ያላነሱ ነጋዴዎችና...
-
አምቡላንሱ የባለስልጣኑን የሰርግ እቃ ሲያመላልስ የነፍሰጡሯ ህይወት አለፈ
አሳዛኙ ዜና የተደመጠው በጎንደር ፎገራ ወረዳ አምባ ጊዮርጊስ ውስጥ ነው፡፡ ‹‹አንዲትም እናት...
ቀጣይ ጽሁፎች
የአንድነት/መድረክ የፖለቲካ ግንኙነት እና የጋራ እንቅስቃሴ ከመቀናጀት እስከ ግንባር ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ግምገማ
ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ብ/ም/ቤት ባደረገው ስብሰባ ላይ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአንድነት/መድረክ የፖለቲካ ግንኙነት እና የጋራ እንቅስቃሴ ከመቀናጀት እስከ ግንባር ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ ገምግሞ አፅድቋል፡፡ ሰነዱም ለመድረክና ለመድረክ አባል ፓርቲዎች እንዲሰጥ፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲያውቁት እንዲሁም ለህዝቡና ለመገናኛ ብዙሃን እንዲሰራጭ በተባለው ውሳኔ መሰረት እነሆ ሰነዱን [...]
ከሙስናው በስተጀርባ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ከኢየሩሳሌም አርአያ በሕወሐት የተፈጠረው የቀውስ ማእበል አድማሱን እየለጠጠ መሔዱን ተከትሎ «ታማኝ» ሆነው በሙስና ሲያገለግሉ የቆዩትን ጭምር እየበላ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በቀዳሚነት የሚያነሱት በጉምሩክ ቁልፍ ስልጣን የነበረውን የሕወሐት አባል ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስን ሲሆን እንዴትና በማን ወደስልጣን እንደመጣ እንዲሁም ምን-ምን ተግባራት ይፈፅምና ያስፈፅም እንደነበረ ምንጮቹ ሂደቱን እንደሚከተለው ይገልፁታል። ገ/ዋህድ በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት [...]
የ“ኢሕአዴግ ደጋፊዎች” መልካም እንቅስቃሴ
ግርማ ካሳ Muziky68@yahoo.com በዳያስፖራ ቀንደኛ የኢሕአዴግ ደጋፊና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች አስተባባሪ የሚባሉት፣ የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል ዋና አድሚን፣ አቶ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ከአዉራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አደመጥኩ። አባ መላ ጠንካራ ትችት በኢሕአዴግ ላይ ሰንዝረዋል። ይሄም ብዙዎችን ሳያስገርም አልቀረም። «አባ መላ፣ አራዳ ነዉ፤ ወያኔ ሊወድቅ ሲል ፍሬቻ አብሮቶ [...]
የቃሊቲው ደብዳቤና የርዕዮት እውነቶች
በስለሺ ሀጎስ ሚያዝያ 23 2005 ዓ.ም ሪፖርተር ጋዜጣ በቅጽ 18 ቁጥር 44/1356 ዕትሙ “በህግ ታራሚ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የደረሰ አንዳችም አይነት ችግር የለም!” በሚል ርዕስ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር የተላከ ደብዳቤ አስነብቧል፡፡ ደብዳቤው በቅጥፈትና በክህደት የተሞላ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ባልተነሳ ጥያቄና ባልተባለ ነገር ላይ በማተት የተነሳበትን ሀቀኛ ጥያቄ አደናብሮ ለማለፍ [...]
በሽብርተኝነት ሰበብ ሀሳብን የመግለፅና የፕሬስ ነፃነትን ማፈን ይቁም!
ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 25 ቀን 2005 ዓ.ም የአለም ፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሯል፡፡ ይህ አለም አቀፍ የጋዜጠኞት በአል ከመከበሩ አንድ ቀን አስቀድሞ የፌደራሉ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች መሰል የህሊና እስረኞች ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ ነበር፡፡ ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩ ውግዘቶችን “ጆሮ ዳባ ልበስ” ያለው ኢህአዴግ [...]
መንግስት በጎንደር የበአል ቆዳ ለማሰባሰብ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀረ
በመላው ህዝበክርስቲያን ለተከበረው የፋሲካ በአል የታረዱ እንስሳትን ቆዳ “ለአባይ ግድብ” ማሰሪያ በሚል ጎንደር ከተማ መስተዳድር ለመሰብሰብ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ እንደቀረ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከጎንደር ዘገቡ፡፡ በአንፃሩ የጎንደር ወጣቶች በከተማዋ ግንባታው በመካሄድ ላይ ላለው የሐዋርያው ዮሃንስ ህንፃ ቤተክርስቲያን ማጠናቀቂያ የሚውል በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ቆዳ ማሰባሰባቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡ እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች [...]
የአለም ፕሬስ ነጻነት ቀን በሀራምቤ ተከበረ
የአለም የፕሬስ ነጻነት ቀን በነፃ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች፣አራማጆችና የፕሬስ ነፃነት ተቆርቋሪዎች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው ሀራምቤ ሆቴል ተከበረ፡፡ በአሉን ለማክበር በማህበረሰብ ገጽ (በፌስ ቡክ ) አማካኝነት በተደረገው ጥሪ መሰረት የተሰባሰቡት ነፃ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች፣አራማጆችና የፕሬስ ነፃነት ተቆርቋሪዎች በሀራምቤ ሆቴል በመገኘት ዕለቱን አክብረዋል፡፡ ‹‹የዘንድሮውን የፕሬስ ቀን የምናከብረው ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያቀረበው የይግባኝ [...]
የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አንዷለም አራጌን እንዳይጠይቁ በልዩ ሀይል ተባረሩ
የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ወጣቱን ፖለቲከኛና የፓርቲው አመራር አንዷለም አራጌን እንዲሁም ሌሎችን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ለመጠየቅ ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ቃሊቲ ቢሄዱም ለመጠየቅ እንዳይችሉ መደረጋቸውንና እስካፍንጫቸው በታጠቁ ልዩ ሃይሎች በግድ ከአካባቢው እንዲርቁ መደረጋቸውን የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አስታወቀ፡፡ እንደፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ገለፃ ከፍተኛው ፍ/ቤት [...]





















